17ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን!

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 86


17ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን!

17ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን! ============== የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት17ኛውን የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦችና ህዝቦች ቀን በዓል በከተማ አስተዳደር ደረጃ በድምቀት ለማክበር ሰፊ ዝግጅት ማድረጉን ገለፀ። ምክር ቤቱ የበዓል አከባበሩ መሪ እቅድ ላይ ዛሬ ከአብይ ኮሚቴው ጋር ተወያይቷል። ውይይቱን የመሩት የምክር ቤቱ አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር እንደገለፁት የዘንድሮው በዓል ህገ-መንግስታዊ አስተምህሮንና ሀገራዊ ምክክሩን በሚያጠናክር መልኩ ይከበራል ብለዋል። በተለይ ይህ በዓል በአዲስ አበባ ሲከበር ከተማችን ትንሿ ኢትዮጵያ መሆኗን በሚያሳይ መልኩ ይሆናል ብለዋል። የበዓሉን መሪ እቅድ የምክር ቤቱ የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ አዲስአለም እንቻለው ያቀረቡ ሲሆን በዓሉ በዋናነት በፓናል ውይይት ፣ በባህል ፌስቲቫል እና በልዩ ልዩ ዝግጅቶች ይከበራል ብለዋል። በውይይቱ ላይ የምክር ቤቱ ከፍተኛ አመራሮች፣ የከተማ አስተዳደሩ ቢሮ ሀላፊዎች ፣የሁሉም ክፍለ ከተማ አፈ ጉባኤዎችና የሚዲያ ሀላፊዎች ተሳትፈዋል። 17ኛው የኢትዮጵያ ብሄሮች ብሄረሰቦች እና ህዝቦች ቀን በዓል "ህብረ ብሄራዊ አንድነታችን ለዘላቂ ሰላማችን!" በሚል መሪ ቃል ህዳር 29/2015 ዓ.ም በሲዳማ ክልል አዘጋጅነት በሀዋሳ ከተማ ይከበራል። ======== ዜና ፕ/ህ/ግንኙነት ዳይሬክቶሬት



Leave a Comment: