የምክር ቤቱ ጽ/ቤት ስልጣን፣ ተግባርና ኃላፊነት፡

የምክር ቤቱ ጽ/ቤት በተሻሻለው አዋጅ ቁ.80/2015 የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ተሰጥተውታል፤ እነዚህም፡

1. ለምክር ቤቱ ህግ አወጣጥ፣ ክትትል ቁጥጥር እና ለሕዝብ ውክልና ሥራዎች የሚያስፈልጉ ሙያዊ ድጋፍና አስተዳደራዊ አገልግሎቶችን ይሰጣል፤

2. በምክር ቤቱ ለሚቋቋም ኮሚቴና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች አጠቃላይ አስተዳደራዊ አገልግሎትና ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤

3. ምክር ቤቱ ያፀደቀውን ሕግ በአዲስ ነጋሪ ጋዜጣ ያሳትማል፣ ያሰራጫል፤ ያስተዳድራል፤

4. የምክር ቤቱን ረቂቅ በጀት አዘጋጅቶ ለአፈ-ጉባኤ ያቀርባል፤ በሚመለከተው አካል ሲፀድቅ ተግባራዊ ያደርጋል፤

5. ለምክር ቤቱ አባላት በህግ የተወሰኑ ጥቅማ ጥቅሞች እና ልዩ መብቶችን ያስፈጽማል፤

6. ለምክር ቤቱና ለምክር ቤቱ የተለያዩ አካላት የቃለ-ጉባዔ፣ የአዳራሽ አገልግሎት፣ የህትመትና ሌሎች የኮንፈረንስ አገልግሎቶችን ይሰጣል፤

7. የምክር ቤቱን ቃለ ጉባዔ እና ውሣኔ ቁጥር እየተሰጠው በሚገባ ተመዝግበው እንዲጠበቁ ያደርጋል፤

8. ለምክር ቤቱ አባላትና ተገልጋዮች የቤተ-መጻሕፍት፣ የምርምር፣ የመረጃና ዶክመንቴሽን አገልግሎት ይሰጣል፤

9. ለምክር ቤቱ አባላትና እንግዶች አስፈላጊውን የመስተንግዶ አገልግሎት እንዲያገኙ ያደርጋል፤

10. የንብረት ባለቤት ይሆናል፤ ንብረቱንም ያስተዳድራል፣ ውል ይዋዋላል፣ በስሙ ይከሳል፣ ይከሰሳል፤

11. ለጽህፈት ቤቱ ሠራተኞች የአቅም ግንባታ ሥራዎችን ይሰራል፤

12. ዓላማውን ለማሳካት የሚረዱ የሕዝብ ግንኙነት፣ የገጽታ ግንባታ እና ሌሎች ተግባራትን ያከናውናል፡፡

ክቡርት ወ/ሮ ጃዋሪያ ቀሊ
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ጽ/ቤት ኃላፊ