3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን 21 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ አጠናቀቀ።

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 31


3ኛው የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ መደበኛ ጉባኤውን 21 ነጥብ 7 ቢሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት በማፅደቅ አጠናቀቀ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበለትን ከ21 ቢሊየን 739 ሚሊየን ብር በላይ ተጨማሪ በጀት አፅድቋል፡፡
በጉባኤው 3ኛ አጀንዳነት የያዘው የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የ2016 በጀት አመት ተጨማሪ በጀት መግለጫን የአዲስ አበባ ፋይናንስ ቢሮ ሀላፊ አቶ አብዱልቃድር ሬድዋን አቅርበዋል ፡፡
የቢሮ ሀላፊው ባቀረቡት ተጨማሪ በጀት ረቂቅ ላይ የከተማ አስተዳደሩ በበጀት አመቱ ለሚያከናውናቸው ልዩ ልዩ ተግባራት 140.29 ቢሊየን ብር በጀት ማፅደቁን አስታውሰዋል ፡፡
ለተጨማሪ በጀቱ መነሻ ታሳቢዎች ውስጥም ባለፉት 9 ወራት የከተማ አስተዳደሩ የነበረው የገቢ አፈፃፀምም ከታክስ ፣ ታክስ ካልሆነ ገቢ እንዲሁም ከማዘጋጃ ቤታዊ ገቢ 108.8 ቢሊየን ብር ገቢ መሰብሰብ የተቻለ ሲሆን ይህም ካለፈው በጀት አመት ተመሳሳይ ጊዜ ሲነፃፀር የ35.5 ቢሊየን ብር ወይም የ32.7 በመቶ እድገት አሳይቷል ብለዋል ፡፡
ለዚህ አፈፃፀም መሻሻል የከተማ አስተዳደሩ የክትትል ድጋፍ ስራ መጠናከር እንዲሁም የማስፈፀም አቅም እያደገ መምጣቱ መሆኑን ቢሮ ሀላፊው አብራርተዋል ፡፡
የከተማ አስተዳደሩን የወጪ ፍላጎት ምላሽ ለመስጠትም የገቢ አፈፃፀሙ በማደጉና በ2015 በጀት አመት ጥቅም ላይ ያልዋለ ሀብት በመኖሩ እንዲሁም ከተለያዩ የገቢ ምንጮች የተገኘና የሚገኝ መሆኑ በመረጋገጡ የሀብት ምደባ ተደርጓል ፡፡
በተደረገው የሀብት ምደባም የወጪ በጀት 21 ቢሊየን 739 ሚሊየን 638 ሺህ 433 ብር ከ32 ሳንቲም በተጨማሪ በጀትነት እንዲፀድቅ ቀርቧል ፡፡
ከዚህ ወጪ ውስጥም ለመደበኛ ወጪ 909 ሚሊየን 253 ሺህ 963 ብር የጠቅላላውን 4.2 በመቶ ፣ ለካፒታል ስራዎች 20 ቢሊየን 830 ሚሊየን 384 ሺህ 470 ከ32 ሳንቲም ወይም የአጠቃላዩን 96 በመቶ ተደግፎ ቀርቧል፡፡
የካፒታል በጀቱ ከፍ ያለበት ምክንያትም በከተማ አስተዳደሩ ትኩረት መሰረት ለተጀመሩ የግንባታ ስራዎች ለመንገድ ለካሳ ክፍያ ለአረንጓዴ ልማትና አካባቢ ጥበቃ ስራዎች ማጠናቀቂያና ለጤና ተቋማት የውስጥ ግብአት ማሟያ ታሳቢ ተደርጎ መመደቡን አብራርተዋል፡፡
በጠቅላላ ከተመደበው በጀት ውስጥ ለማእከል ሴክተር መስሪያ ቤቶች 19 ቢሊየን 763 ሚሊየን 62 ሺህ 26 ከ05 ሳንቲም የተመደበ ሲሆን ከአጠቃላይ በጀቱ 91 በመቶ ድርሻ አለው፡፡
ለክፍለ ከተሞችም 1 ቢሊየን 976 ሚሊየን 576 ሺህ 407 ከ27 ሳንቲም ይህም ከከተማዋ አጠቃላይ ወደ 9.1 ድርሻ ይይዛል ብለዋል፡፡
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በተሻሻለው የፋይናንስ አስተዳደር አዋጅ መሰረት የከተማ አስተዳደሩ ያቀረበውን ተጨማሪ በጀት ምክር ቤቱ ተቀብሎ በሙሉ ድምፅ ጉባኤውን አጠናቋል ፡፡
የህ/ግ/ኮ/ዳይሬክቶሬት
ሚያዝያ 18/2016 ዓ.ም



Leave a Comment: