የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ተኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 28


የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ ዓመት የስራ ዘመን 3ተኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ይገኛል።

ምክር ቤቱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የኮሪደር ልማትና የአድዋ ዙሪያ መልሶ ማልማት እቅድ አፈፃፀም ሪፖርት በክብርት ከንቲባ ወ/ሮ አዳነች አበቤ ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል ።
ከንቲባዋ በሪፖርታቸው በምርጫ 2014 ወቅት እንደ ብልፅግና ፓርቲ በአዲስ አበባ ለህዝባችን የገባዉን ቃል ወደ ተግባር በመቀየር አዲስ አበባን፣ እንደ ስሟ አበባ ፅዱ፥ ለነዋሪዎችዋ ምቹ፣ በከተማ ፕላን የምትመራና የተሟላ የከተማ ስርዓት ያላትና፤ ለአፍሪካ ከተሞች የብልጽግና ተምሣሌት ለማድረግ የያዝነውን ራዕይ እዉን እንዲሆን ባደረግናቸዉ ያላሰለሰ ጥረት በርካታ ተስፋ ሰጪ ዉጤቶችን ማስመዝገብ መጀመራቸውን ገልፀዋል፡፡
ከንቲባዋ አክለው እንደገለፁት በ5ቱም የኮሪደር ልማት ከመኖሪያ ቤት እስከ መስሪያ ቦታዎች 5.135 በማንሳት ቦታውን አፅድቶ ለልማት ዝግጁ ማድረግ ሲቻል እስካሁን ለ4000 (80%) የልማት ተነሽዎች ካሳ ምትክ ቦታ፣ ምትክ ቤትና ምትክ የመስሪያ ቦታ በመስጠት እንዲስተናገዱ በማድረግ ለ307 የግል ይዞታ ተነሺዎች 2.8 ብር ካሣ ፀድቆ 1.5 ቢሊዮን ብር ካሳ መክፈል መቻሉን ገልፀው ;ለ417 የቀበሌ ንግድ ቤቶች እና ለ393 ለፌዴራል ኪራይ ቤቶች በድምሩ ለ1.117 የግልና የመንግስት ባለይዞታዎች 30 ሔክታር ምትክ መሬት ተዘጋጅቶ እየተስተናገዱ መሆኑን ገልፀዋል።
የመዲናዋ የኮሪደር ልማት 48.7 ኪሜ የሚሽፍን እና በተመረጡ የከተማችን አምስት ኮሪደሮች ከ4 ኪሎ ፒያሳ የአድዋ ድል መታሰቢያ ዙሪያ መልሶ ማልማት ከ4 ኪሎ አደባባይ በእንግሊዝ ኤምባሲ በመገናኛ፣ ከሜክሲኮ ሳር ቤት በጎተራ ወሎ ሰፈር አደባባይ፣ ከአራት ኪሎ መስቀል አደባባይ እና ከቦሌ ድልድይ፣ በመገናኛ አስከ አዲስ አፍሪካ ኮንቬንሽን እግዚቢሽን ማእከልን ያካተተ መሆኑን ከንቲባዋ በሪፖርታቸው ገልፀዋል።
ክብርት ከንቲባዋ ከምክር ቤት አባላት ለቀረበላቸው የግልፀኝነት ጥያቄ በሰጡት ማብራሪያ የመልሶ ማልማት ስራ የአለም አቀፍ በሀገራችን የነበረ ተሞክሮ መሆኑን ጠቅሰው የአሁኑን ለየት የሚያደርገው ከመልሶ ልማቱ በተጨማሪ የከተማዋን ገፅታ የማይመጥኑና ለነዋሪዎቿ ምቹ ያልሆኑ አካባቢዎችን አጥንተንና ለይተን በኮሪደር ልማት የነዋሪውንና የእንግዷቿን ፍላጎት ለመኖሪያና ለመዝናኛነት የሚሆኑ ልማቶችን ያካተተ መሆኑ ነው ብለዋል። በመጨረሻም ከንቲባዋ ነዋሪ ለኮሊደር ልማቱ ያሳየውን ቀና ትብብር ምስጋና አቅርበው የቀረበው ሪፖርት በሙሉ ድምፅ ፀድቋል።
ሚያዚያ 18/2016 ዓ/ም



Leave a Comment: