የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አመራር እና አባላት በመዲናዋ እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎበኙ::

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 30


የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት አመራር እና አባላት በመዲናዋ እየተሰሩ ያሉ የኮሪደር ልማት ስራዎችን ጎበኙ::

አዲስ አበባ ከተማ የአለም አቀፍ ተቋማትና የበርካታ ሀገራት የዲፕሎማት መቀመጫ በመሆኗ የአፍሪካ መዲና ቢያሰኛትም በከተማዋ የተቀናጀ የመሰረተ ልማት አቅርቦት አለመኖር በከተማዋ እድገትና ስልጣኔ ብሎም ለነዋሪዎቿና ለእንግዶቿ ምቹ አለመሆን በምክንያትነት ይጠቀሳል::
ይህን የከተማዋን ስር የሰደደ የዘመናት ችግር ከስሩ ለመቅረፍ በከተማ አስተዳደሩና በሀገር አቀፍ ደረጃ አጭርና እረጅም የመንግስት ስትራቴጅክ እቅድ ነድፎ በዘላቂ የመሰረተ ልማት ግንባታና አቅርቦት ላይ በልዩ ትኩረት እየሰራ ይገኛል::
የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የዚሁ ከተማዋን ለነዋሪዎቿ ምቹ የማድረግና በተቀናጀ የመሰረተ ልማት የማዘመን አንዱ አካል የሆነውን የኮሪደር ልማት ስራዎች በምክር ቤቱ አፈጉባኤ እየተመራ ጉብኝት አካሂዷል::
የምክር ቤት አባላቱ የተሰሩ ስራዎችንና በልማቱ ተያያዠ ስራዎች ከመኖሪያቸው የተነሱ የከተማዋን ነዋሪዎች ያሉበትን ሁኔታ በሀና ፉሪና አቃቂ ቃሊቲ ተገጣጣሚ ቤቶች ተዘዋውሮ ተመልክቷል::
በጉብኝቱ የተከበሩ ወ/ሪት ፋኢዛ ሙሀመድ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ-ጉባኤ እንደተናገሩት የኮሪደሩ ልማት ከተማዋን የሚያዘምንና ካደጉ ሀገራት ተወዳዳሪነቷን የሚያረጋግጥ በመሆኑ አሁን ላይ በተያዘለት ጊዜና ጥራት ለማጠናቀቅ ቀን ከሌት እየተሰራ ስለመሆኑን ከምክር ቤቱ አባላት ጋር ተዘዋውረው ማረጋገጣቸውን ገልፀዋል::
በተመሳሳይ የከንቲባ ጽ/ቤትና የካቢኔ ጉዳዮች ም/ኃላፊ አቶ መኮንን ያኢ እንዳሉት ለተነሽዎች የይዞታ፣ የስነ ልቦናና የትራንስፖርት ግምትን ያገናዘበ የካሳና ተመጣጣኝ የመኖርያ ቤት እንደ ተነሽዎች አቅምና ፍላጎት መሰጠቱን ገልፀው ነዋሪዎቹ የመሰረተ ልማት አቅርቦት ችግር እንዳይገጥማቸው ቤቶቹ ከመሰጠታቸው በፊት የትምህርት፣ የጤና፣ የመብራትና የውሃ መሰረተ ልማት መሟላታቸውን ገልፀዋል::
የኮሪደር ልማቱ በከተማዋ አምስት ዋና ዋና መስመሮች 40.75 ኪ/ሜ መንገድ የሚያካትት ሲሆን በውስጡ የአስፖልት መንገድ ግንባታና ማሻሻያ፣ የህንፃ ከፍታ ምጣኔ, የህንፃ ቀለም ኮድ፣ የእግረኛና የሞተር አልባ ተሽከርካሪዋችና አረንጓዴ ልማት፣ የንግድ ማዕከላት፣ የትራንስፖርት ተርሚናሎች፣ የህጻናት መጫወቻ፣ መጸዳጃ ቤቶች እና ፓርኪንጎችን ያካተተ መሆኑን ለማየት ተችሏል ።
በተመሳሳይ በጉብኝቱ የተሳተፉ የምክርቤት አባላት በበኩላቸው አዲስ አበባ ዳግም የመወለድ ያህል ለውጥ ላይ መሆኗን ጠቁመዋል።
በብርቱካን አህመድ
ሚያዝያ 17/2016 ዓ.ም



Leave a Comment: