ምክር ቤቱ ለወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 32


ምክር ቤቱ ለወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡

ምክር ቤቱ ለወረዳ ምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና ሰጠ፡፡ የህዝብ እንደራሴ የሆኑ የምክር ቤት አባላት የነዋሪውን ህዝብ አንገብጋቢ የመልካም አስተዳደር ቁልፍ ችግሮች በመለየትና በመፍታት ሂደት ግምባር ቀደም ተዋናይ ናቸው። በዚህ ረገድ ምክር ቤቶች ህዝብ የጣለባቸውን ኃላፊነት በቅጡ ይወጡ ዘንድ ግዜው የሚጠይቀውን እውቀትና ክህሎት መላበስ ቅድሚያ የሚሰጠው ተግባር በመሆኑ የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ከላይ እስከ ታች ላሉ የምክር ቤቱ መዋቅር አመራሮች የአቅም ግንባታ ስልጠና እየሰጠ ይገኛል፡፡
ምክር ቤቱ ለወረዳ የምክር ቤት አፈ ጉባኤዎች በወረዳ ምክር ቤት ስልጣንና ተግባር ላይ ያተኮረ የአቅም ግንባታ ስልጠና የሰጠ ሲሆን የስልጠናውን ዓላማ በመድረኩ መክፈቻ ያብራሩት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ክንፈ አዲስ እንደገለፁት ምክር ቤቱ ከከተማ እስከ ወረዳ በሶስት ደረጃ የተዋቀረ ሲሆን ህዝቡን በተግባር የሚያገኘው የወረዳ የህዝብ እንደራሴዎች የመረጣቸውን ህዝብ ያለድካም ለረጅም ጊዜ ያገለገሉ መሆናችናቸውን ጠቅሰዋል። በቀጣይም የሚሰሩ ስራዎች በተሻለ ውጤት ይታጀቡ ዘንድ በክህሎትና በእውቀት እንዲመራ ይህ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና መዘጋጀቱን ጠቁመው ተሳታፊዎች ከስልጠናው ግብዓት ወስደው የወከላቸውን ህዝብ በተሻለ አቅም እንዲያገለግሉ ጥሪያቸውን አቅርበዋል፡፡
የስልጠናውን ጭብጥ ለተሳታፊዎች ያቀረቡት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የክትትልና ቁጥጥር ከፍተኛ ባለሙያ የሆኑት አቶ ፒተርዘግሬት ለይኩን እንዳሉት ምክር ቤቶች በህገመንግስት አንቀፅ 4(1) መሰረት ለህገ መንግስቱ፣ ለህዝቡና ለህሊናቸው መገዛት ኃላፊነት እንዳለባቸው ጠቅሰው የወረዳ ምክር ቤቶች የወረዳውን ኤኮኖሚያዊ ማህበራዊ ልማትና የማዘጋጃ ቤት አገልግሎትን ማፅደቅ፣ የወረዳውን በጀት ማፅደቅ፣ አስፈፃሚውን አካል መከታተልና መቆጣጠር ስልጣን ያለው መሆኑን ገልፀው የህዝብ እንደራሴዎች የመረጣቸው ህዝብ ለጣለባቸው ኃላፊነት መገዛት ግዴታ አለባቸው ብለዋል፡፡
በነፃነት ብርሃኑ
መጋቢት 21/2016 ዓ/ም



Leave a Comment: