የአዲሱ ምእራፍ ምክር ቤት የስራ ዘመኑን አጋማሽ የስራ አፈፃፀም ገመገመ፡፡

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 72


የአዲሱ ምእራፍ ምክር ቤት የስራ ዘመኑን አጋማሽ የስራ አፈፃፀም ገመገመ፡፡

የአዲሱ ምእራፍ ምክር ቤት አፈ ጉባኤ የተከበሩ ወ/ሮ ቡዜና አልከድር የአምስት አመት የስራ ዘመን አጋማሽ የስራ አፈፃፀም ሪፖርት ለምክር ቤቱ አቅርበዋል፡፡ አፈ ጉባኤዋ በመግቢያ ንግግራቸው እንደገለፁት የሰራ ዘመናችን አጋማሽ እንደመሆናችን ባሳለፍነው የስራ ዘመን የሰራናቸውን አንኳር ጉዳዮች በመልካም አፈፃፀም የለየናቸውን አፈፃፀሞች አስቀጥለን የቀሩንን ስራዎች በቀሪ የስራ ዘመን ከምክር ቤት አባላቱ ግብዓት ወስደን በጋራ መክረን በህዝብ ይሁንታ የተመረጥንበትን የህዝብ እንደራሴነታችንን በውል እናሳያለን ብለዋል፡፡ አፈ ጉባኤዋ በሪፖርታቸው በትኩረት ካነሷቸው አንኳር ነጥቦች በዋናነት ምክር ቤቱ በምርጫ ዘመን አጋማሽ ቆይታው ባደረጋቸው አፈፃፀሞች የተገኙ ውጤቶችን ሲያብራሩ ህግ የማውጣትና የአሰራር ስርዓት በማሳደግ ረገድ 17 (አስራ ሰባት) ከተማ አቀፍ አዋጆችና ደንቦችን የማውጣትና የወጡ ህጎችን የማሻሻል ስራ ከመስራት ባሻገር በየደረጃው ባሉ አስፈፃሚ ተቋማት ተግባራዊነቱን የማረጋገጥ ስራ ሲሰራ በተቋማት ክትትል ቁጥጥርና ድጋፍ በማድረግ ግልፀኝነትና የተጠያቂነት አሰራር ስርዓት በማሳደግ በቻርተሩ በተሰጠው ተግባርና ኃላፊነት መሰረት በአስፈፃሚ አካላት ክትትል ቁጥጥርና ድጋፍ በማድረግ በምርጫ ዘመኑ አጋማሽ ጊዜ ውስጥ 2 ጊዜ ዕቅድ ግምገማ፤ 8 ጊዜ የሪፖርት ግምገማ፤ 4 ጊዜ የመስክ ምልከታ እና 4 ጊዜ መደበኛ ሱፐርቪዥን ስራዎች መሰራቸውን ገልፀዋል፡፡ የህዝብ ግንኙነት፣ የመረጃ ተደራሽትና ገጽታ ግንባታ ስርዓትን ከማሳደግ አንፃር ባለፉት ሁለት ዓመት ተኩል ጊዜ የተካሄዱ ሁሉም ጉባኤዎች በአዲስ ሚዲያ ኔትዎርክ የቀጥታ ስርጭት ሽፋን እንዲያገኝ ሲደረግ፤ በሌሎች የግልና የመንግስት ሚዲያ ተቋማት የዜናና የዘገባ ሽፋን እንዲያገኙ በማድረግ ለከተማው ነዋሪ የምክር ቤቱን የጉባኤ ሂደት ተደራሽ መደረጉን ገልፀው የምክር ቤቱ የቋሚ ኮሚቴዎች የተቋማት የመስክ ምልከታ፣ የሕዝብ ውይይት መድረኮች፣ የኮከስ፣ የትስስር አደረጃጀቶች፣ የኦዲት ፎረም እና ሌሎች የምክር ቤት አካላት አፈጻጸሞችን መረጃዎች በተለያዩ የሚዲያ አማራጮች ተደራሽ በማድረግ የብሄራዊ በዓላትና ሌሎች ሁነቶችን በመጠቀም የዴሞክራሲ ስርዓት ግንባታን ለማጠናከር ምክር ቤቱ በልዩ ትኩረት ስራዎች መሰራታቸውን ገልፀዋል፡፡ አፈ ጉባኤዋ አክለው እንደገለፁት ምክር ቤቱ በሰራቸው አንኳር ስራዎች የተገኙ ውጤቶችን ሲያብራሩ በለተቋማት አገልግሎት አሰጣጥ ማነቆ የሆኑና ቅሬታ የሚፈጥሩ አሰራሮችን በማሻሻል ተቋማቱ የአገልግሎት አሰጣጣቸውን በማዘመን የዘገዩ ወይንም የቆሙ የግንባታ ፕሮጀክቶች በተፈቀደ በጀትና በተቀመጠላቸው ጊዜ በማጠናቀቅ ለታለመላቸው አገልግሎት ማብቃትና ህገ ወጥ አሰራሮች እንዲታረሙ በማድረግ የመልካም አስተዳደርና ቀልጣፋ የአገልግሎት አሰጠጥ እንዲኖር በማድረግ ፤ የሕዝብ እሮሮ ምክንያት የሆኑ የአገልግሎት አሰጣጥ ችግሮች እንዲቀረፉና የዋጋ ንረት ብሎም የኑሮ ውድነት እንዲረጋጋ በማድረግ በኩል ምክር ቤቱ ጉልህ ሚና ተጫውቷል ብለዋል፡፡ ክብርት አፈጉባኤዋ በሰጡት የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫ እንደገለፁት፤ የመራጩን ሕዝብ ተጠቃሚነት ማዕከል ያደረገ የህግ ማውጣት፣ ጠንካራ ተከታታይነት ያለው ውጤታማ ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ የተጠያቂነትን አሰራ ስርዓት ማስፈን፤ አሰራሩ የዘመነና በቴክኖሎጂ የታገዘ ተልዕኮ በመፈፀምና የፍትህ ሪፎርም በተሟላ አቅም በመደገፍ ጠንካራ ተቋማዊ የትስስር አጋርነት መፍጠር ምክር ቤቱ በቀጣይ በልዩ ትኩረት የስራል ብለዋል፡፡ በነፃነት ብርሀኑ



Leave a Comment: