" ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል " በሚል መሪ ሃሳብ 20ኛዉ አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች አከበሩ።

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 29


" ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል " በሚል መሪ ሃሳብ 20ኛዉ አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች አከበሩ።

" ሙስና የጋራ ጠላታችን ነው በህብረት እንታገል " በሚል መሪ ሃሳብ 20ኛዉ አለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ፅ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች አከበሩ። ============== የአለም አቀፍ የፀረ-ሙስና ቀን በሀገር አቀፍ ደረጃ ለ19ኛ ጊዜ በተለያዩ ተቋማት እየተከበረ ይገኛል። በዝግጅቱ የዉይይት መነሻ ፅሁፍ ያቀረቡት የስነምግባርና ፀረሙስና ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ማናየ አባይ የዓለም አቀፋ ማህብረሰብ የሙስናን አስከፊነት በመረዳት በህብረት ለመወጋት የተባበሩት መንግስታት ዓለም አቀፍ የፅረ ሙስና ቃልኪዳን ስምምነት ከገቡበት ቀን ጀምሮ ሙስናን ለመከላከልና ለመግታት በርካታ ስራዎች መሠራታቸውን ገልፀው; ሃገሪቱ ሙስናን ለመታገል የሚያስችሉ የህግ ማዕቀፎች፣ ተቋማት እና እቅዶች ተግባራዊ ብታደርግም ችግሩ ግን የሀገሪቱን የልማት፣ የዲሞክራሲ እና የመልካም አስተዳደር ቁልፍ ችግሮች መንስዔ ሆኖ ቀጥሏል ብለዋል፡፡ ሰነዱን መሠረት በማድረግ ውይይቱን የመሩት የአፈ ጉባኤ አማካሪ አቶ ሞላ ንጉስ እንደ ከተማ ፅረ ሙስና ያልተገባ በረካታ የተወሰዱ ንብረቶች በማስመለስ ረገድ ጥሩ እርምጃ መውሰዱን ገልፀው የፖለቲካ አመራሩ ቁርጠኝነት መኖር መሠረታዊ ጉዳይ እንደሆነና ጠንካራ የፅረ ሙስና ህግና አስፈፃሚ አካል እንዲኖር ማድረግ እንዲሁም ጠንካራ የሲቪል ማህበረሰብ መፍጠር በፅረሙስና ትግሉ ውጤታማ የሚያደረጉ ስልቶች እንደሆኑ ጠቁሟል ። የፅ/ቤቱ አመራሮችና ሰራተኞች በቀረበው የግንዛቤ ማስጨበጫ ሰነድ ላይ የተለያዩ ሀሳቦችና አስተያየቶች አንስቶ ሰፊ ውይይት አድረጓል ። ሙስና፣ ግጭቶችና መፈናቀሎች ተመጋጋቢ ችግሮች መሆናቸዉን የተለያዩ ጥናቶች ያመለክታሉ፡፡ እንደ ዓለም ባንክ (2018) ጥናት በዓለማችን ላይ በአንድ ዓመት ጊዜ ዉስጥ አንድ ትሪሊዮን የአሜርካን ዶላር በጉቦ መልክ የሚባክን ሲሆን፣2.6 ትሪሊዮን ዶላር በተለያዩ የሙስና ወንጀል ድርጊቶች ይሰረቃል፡፡ ========= ህዳር 20/2016ዓ.ም የህ/ግ/ኮ/ዳይሬክተር



Leave a Comment: