በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት "የሴት ምክር ቤት አባላት ኮከስ" ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 38


በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት "የሴት ምክር ቤት አባላት ኮከስ" ጉባኤውን እያካሄደ ነው።

በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት "የሴት ምክር ቤት አባላት ኮከስ" ጉባኤውን እያካሄደ ነው። AMN- ህዳር 16/2016 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት "የሴት ምክር ቤት አባላት ኮከስ" 3ኛ ዓመት የሥራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤውን እያካሄደ ነው። "የሴት ምክር ቤት አባላት ኮከስ" የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የተደራጀ አደረጃጀት ሲሆን ባለፉት ግዜያት ያከናወናቸውን ተግባራት መነሻ አድርጎ ጉባዓውን እያካሄደ ነው። በጉባኤው መክፈቻ ላይ መልዕክት ያስተላለፉት የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት ምክትል አፈ-ጉባኤ ወ/ሪት ፋኢዛ መሐመድ ኮከሱ የሴቶች ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተጠቃሚነት እንዲረጋገጥ እንዲሁም በዴሞክራሲ ሥርዓት ግንባታ ዘርፎች ላይም ተሳትፎአቸውን ለማጠናከር የተቋቋመ አደረጃጀት መሆኑን ጠቅሰው ተግባሩ ተጠናክሮ እንዲቀጥል አፅንኦት ሰጥተዋል። ኮከሱ በ2016 በጀት ዓመት የዕቅድ አፈጻጸም ላይ ያከናወናቸውን ተግባራት እየገመገመ ይገኛል። በወገን ታከለ



Leave a Comment: