የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 29


የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት 3ኛ የስራ ዘመን 1ኛ መደበኛ ጉባኤ አዋጅ ቁጥር 016/2016ዓ.ም የአስፈፃሚ አካላት ለማቋቋም የወጣ አዋጅ አፀደቀ። ረቂቅ አዋጅ ለከተማው ህዝብ ተጠቃሚነት ሲባል ተግባራትን ከማከናወን አኳያ ከተማ አስተዳደሩ አዋጅ ቁጥር 361/95 በተሰጠው ስልጣንና ተግባር በእኩልነትና በግልፅነት መርህ መሠረት አንቀፅ14 ንዕስ አንቀፅ (1 )ተራ ፊደል ሀ መሠረት አዋጅ ማውጣቱን ተገልፀዋል። ተጠሪነታቸው ለከንቲባ የሆኑት ; የህብረት ስራ ኮሚሽን፣ የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ፣ የውሃና ፍሳሽ ባለስልጣን ፣የመንግስት ልማት ድርጅቶች አሰተዳደር ባለስልጣን እና የመስሪያ ቦታዎች ልማትና አስተዳደር ኤጄንሲ ሲሆኑ ኢንዱስትሪ ልማት ቢሮ የስራና ክህሎት ቢሮ፣ የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የሕብረተሰብ ተሳትፎና በጎ ፋቃድ ማስተባበርያ ኮምሽን ፣የግንባታ ፍቃድና ቁጥጥር ባለስልጣን እና የመንግስት ልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ደግሞ በካብኔ አባላት ውስጥ የገቡ መሆናቸውን በአዋጅ ቀርበዋል ። በተመሳሳይ እንደገና የተቋቋመው አስፈፃሚ አካላት እንዱስትሪ ልማት ቢሮ፣ የስራ ክህሎት ቢሮ፣ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ልማት ቢሮ፣ የፕላንና ልማት ቢሮ፣ የመንግስት የልማት ድርጅቶች አስተዳደር ባለስልጣን ፣የህብት ስራ ኮምሽን ፣የምግብና መድሀኒት ባለስልጣን ፣የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን እንዲሁም የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጄንሲ ና የመስሪያ ቦታዎች ልማት አስተዳደር ኤጄንሲ መሆኑን ተገልፀዋል። በመጨረሻም የሲቪል ምዝገባና የነዋሪዎች አገልግሎት ኤጄን ሲ ና የመስሪያ ቦታዎች ልማት አስተዳደር ኤጄንሲ ለከተማ ስራ አስኪያጅ ተጠሪ ሲሆን የትራፊክ ማኔጅመንት ባለስልጣን ለትራንስፖርት ቢሮ ተጠረ ተቋም እንዲሆኑ ምክርቤቱ በሙሉ ድምፅ አፅድቆታል ። የህ/ግ/ኮ/ዳይሬክቶሬት ህዳር 15/2016ዓ.ም



Leave a Comment: