የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት ምልከታ ማጠቃለያ ግብረ መልስ የጋራ አደረገ።

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 38


የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት ምልከታ ማጠቃለያ ግብረ መልስ የጋራ አደረገ።

የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና የትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ የተቋማት ምልከታ ማጠቃለያ ግብረ መልስ የጋራ አደረገ። ======================= ቋሚ ኮሚቴው በሚከታተላቸው ሴክተር መስሪያ ቤቶችና ተጠሪ ተቋማት የዝግጅት ምዕራፍና የመጀመሪያ ሶስት ወራት የተግባር ምዕራፍ አፈፃፀም ምልከታ አድርጓል። በምልከታው ስትራቴጂካል ግብ ተኮር የዕቅድ ዝግጅትና አፈፃፀም ላያ ትኩረት ያደረገ የመስክ ምልከታ ያካሄደ ሲሆን የአፈፃፀም እና የቀጣይ የትኩረት አቅጣጫዎች በመስክ በምልከታው ሂደት ተሰጥቷል። የአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የመሰረተ ልማትና ትራንስፖርት ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ የተከበሩ አቶ ክንፈ አዲስ በመስክ ምልከታ ማጠቃለያ ግብረ መልስ የጋራ በተደረገበት ወቅት እንደገለፁት ተቋማት በእቅድ የያዟቸው ተግባራት የከተማ አስተዳደሩን ነዋሪዎች ዘላቂ የሆነ የመሰረተ ልማት አቅርቦትና አዳጊ የአገልግሎት ፍላጎት መላሽ ሰጭ በሆነ መልኩ መሰራት አለመሰራታቸውን ቋሚ ኮሚቴው በመስክ ምልከታው በትኪረት መገምገም መቻሉን ገልፀው ተቋማቱ የመሰረተ ልማት አቅራቢ ተቋማት እንደመሆናቸው የሚገነቡ የመሰረተ ልማቶች በዘላቂ የመሰረተ ልማት አቅርቦትና አስተዳደር ላይ ትኩረት አድርገው እንዲሰሩ ቋሚ ኮሚቴው የተቋማትን ድጋፍ ክትትልና ቁጥጥር አጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። ሰብሳቢው አክለው እንደገለፁት ተቋማቱ በዚህ የዝግጅት ምዕራፍና የመጀመሪያ ሶስት ወራት አፈፃየተሻሉ አፈፃፀሞች መኖራቸውን ገልፀው ተቋማቱ በጥንካሬ የተለዩ ተግባራትን በማስቀጠል የአፈፃፀም ክፍተት ያሳዩ ተግባራትን በመለየት ለተሻለ አፈፃፀም መብቃት እንደሚገባ ገልፀው ተቋማቱ የምክር ቤቱን ድጋፍ በሚሹ ጉዳዮች ላይ ማድረግ የሚገባውን ድጋፍና ክትትል ያደርጋል ብለዋል። ===================== የህ/ግንኙነትና ኮምንኬሽን ዳይሬክቶሬት ህዳር 13/2016ዓ.ም



Leave a Comment: