የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

Share: Facebook | Twitter | Whatsapp | Linkedin Visits: 39


የሴቶች፣ወጣቶችና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ

ቋሚ ኮሚቴው በተቋማት ላይ እያደረገው ያለው ምልከታ ዛሬም ቀጥሎ ውለዋል። ============== በአዲስ አበባ ከተማ ምክር ቤት የሴቶች፣ ህፃናትና ማህበራዊ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ አዲስ በሚድያ ኔትወርክ ላይ ምልከታ አደረገ፡፡ ቋሚ ኮሚቴው በጣቢያው በመገኘት ተቋሙ አዲስ ያስገባውን ቨርቿዋል ስቱዲዮና ሌሎች የስራ ክፍሎችን ተዛዋውሮ የተመለከተ ሲሆን የቴሌቭዥን ጣቢያው በቴክኖሎጂና በይዘት ባደረገው ለውጥ ተደማጭነቱን በመጨመር ከእቅድ በላይ ገቢ ማስገባት መቻሉ የቋሚ ኮሚቴው ሰብሳቢ የተከበሩ ወ/ሮ ዘይነባ ሸኩር የሚበረታታ መሆኑን ገልፀዋል ። ጣብያው የሪፎርምና ማስፍፊያ ስራ ላይ በመሆኑ በከፍተኛ ወጪ ወጥቶባቸው የተገዙ ግብአቶችን ረጅም ግዜ አገልግሎት እንዲሰጡ ለመቀጠልና ለማስቀጠል ጥንቃቄ ማደረግ እንዳለባቸው ቋሚ ኮሚቴው ጠቁሟል። አክለውም የጋዜጠኞችን አቅም ከመገባት አንፃር የተሰጡ ስልጠናዎች ለተሻለ አቀራረብ እና እውቀት እንዲሚያግዛቸው ገልፀው ቀጣይነት ሊኖረው እንደሚገባም ተናግሯል ። በተጨማሪም ሚድያው ተደማጭ እና ተመራጭ ለማድረግ በተለይ የመልካም አስተዳደር ችግር ያለባቸውን ተቋማት በመለየት የምርመራ ጋዜጠኝነት በማናጠከር የህብረተሰቡ አይንና ጆሮ ሁኖ መስራት ይጠበቅባችኋል ሲሉ አሳስበዋል ። ============= ህዳር13/2016ዓ.ም የህ/ግ/ኮ/ዳይሮክቶሬት



Leave a Comment: