የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት የከተማው ህዝብ የሉዓላዊነት መገለጫና የከተማው ከፍተኛ የሥልጣን አካል ነው፡፡ ም/ቤቱ በቻርተሩ በተሰጠው የሥልጣን ከተማ አቀፍ ህጎችን ያወጣል፤ የወጡትንም ህጎች ተግባራዊነት ይቆጣጠራል፣ይከታተላል፡፡ የአስፈጻሚ አካላትን ዕቅድና አፈፃፀም በመገምገም፣ በመከታተልና በመቆጣጠር ለከተማዉ ነዋሪዎች የሚሰጡ አገልግሎቶች ተግባራዊ መሆናቸዉን በማረጋገጥና የም/ቤቱን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ለከተማው ነዋሪ ተደራሽ በማድረግ መልካም አስተዳደር እንዲሰፍን የበኩሉን ሁሉ ጥረት እያደረገ ይገኛል፡፡ ... ምክር ቤቱ ህግ በማውጣት ክትትልና ቁጥጥር በማድረግ ሂደትም የአዲስ አበባ ከተማ ም/ቤት ጽ/ቤት አስተዳደራዊ ድጋፍ የመስጠት ተግባሩን ያከናውናል፤ በመሆኑም ምክር ቤቱ ከተማዋ ለጀመረቻቸው ለዉጥ የዲሞክራሲ ስርአት ግንባታዎች፣ ለፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማት እንዲሁም ለመልካም አስተዳደር መስፈን የሚረዱ ተጨባጭ ሁኔታ ከህገ-መንግስቱ ጋር የሚጣጣሙ ህጎችን በማውጣት ስራ ላይ እንዲውሉ ያደርጋል። የምክር ቤት ጽ/ቤቱ ለአመራሩና ለቋሚ ኮሚቴዎች አስፈላጊውን አስተዳደራዊ ድጋፍ በማድረግ በአስፈጻሚ አካላት ላይ የክትትልና ቁጥጥር ስራው የተሻለ እንቅስቃሴ መኖሩ፤ የመራጩን ህዝብ ጥያቄ በማንሳት አስፈጻሚዉ አካል ምላሽ እንዲሰጥ መደረጉና የተሰሩ ስራዎች ለህብረተሰቡ ተደራሽ በማድረግ እንዲሁም ም/ቤቱ በቻርተሩ በተሰጠው ሥልጣን ከተማ አቀፍ ህጎችን ያወጣል፤ የወጡትንም ህጎች ተግባራዊነት ይቆጣጠራል፣ይከታተላል፡፡